La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከቀ​ንም ወደ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ከሁ​ለት ዓመት በኋላ ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀቱ ወጣ፤ በክ​ፉም ደዌ ሞተ። ሕዝ​ቡም ለአ​ባ​ቶቹ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ ለእ​ርሱ የመ​ቃ​ብር ወግ አላ​ደ​ረ​ገም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕመሙም ሲያሠቃየው ከቈየ በኋላ፣ በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ በዚሁ ሳቢያ አንጀቱ ወጥቶ በከባድ ሥቃይ ሞተ። ሕዝቡም ለአባቶቹ ክብር እሳት ያነድዱ ነበር፤ ለርሱ ግን አላነደዱለትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከቀንም ወደ ቀን እንዲህ ሆነ፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀቱ ወጣ፥ በክፉም ደዌ ሞተ። ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርገው እንደ ነበረ ለእርሱ የመቃብር ወግ አላደረገም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕመሙም ለሁለት ዓመት ያኽል እየጸናበት ስለ ሄደ አንጀቱ ወጥቶ በብርቱ ሥቃይ ሞተ፤ በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ሕዝቡ ለቀድሞ አባቶቹ ይደረግ በነበረው ወግ ዐይነት ስለ ክብሩ እንጨት ከምረው እሳት አላነደዱለትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከቀንም ወደ ቀን እንዲህ ሆነ፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀቱ ወጣ፤ በክፉም ደዌ ሞተ። ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርገው እንደ ነበረ ለእርሱ የመቃብር ወግ አላደረገም።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 21:19
4 Referencias Cruzadas  

ለእ​ር​ሱም ለራሱ በሠ​ራው መቃ​ብር በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ በቀ​ማሚ ብል​ሃት የተ​ሰ​ናዳ ልዩ ልዩ መል​ካም ሽቱ በተ​ሞላ አልጋ ላይም አኖ​ሩት፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የቀ​ብር ሥር​ዐት አደ​ረ​ጉ​ለት።


አን​ተም ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀ​ትህ በየ​ዕ​ለቱ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በክፉ የአ​ን​ጀት ደዌ ትታ​መ​ማ​ለህ።”


ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


ነገር ግን በሰ​ላም ትሞ​ታ​ለህ፥ ከአ​ንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገ​ሥ​ታት አባ​ቶ​ችህ እሳት ይቃ​ጠ​ል​ላ​ቸው እንደ ነበር እን​ዲሁ ያቃ​ጥ​ሉ​ል​ሃ​ልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ እኔ ቃልን ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።