La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 18:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን ጦር​ነት በረታ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በሶ​ር​ያ​ው​ያን ፊት እስከ ማታ ድረስ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ራሱን ይደ​ግፍ ነበር፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ሞተ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጦርነቱም ቀኑን ሙሉ ተፋፍሞ ዋለ፤ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ እስከ ምሽት ድረስ ተደግፎ ነበር፤ ፀሓይ ስትጠልቅም ሞተ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ቀን ጦርነቱ በረታ፤ የእስራኤልም ንጉሥ በሶርያውያን ፊት እስከ ማታ ድረስ በሠረገላው ላይ ራሱን አስደግፎ ተንጋለለ፤ ፀሐይም በጠለቀች ጊዜ ሞተ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ይታይ ነበር፤ ፀሐይ ስትጠልቅም ሞተ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቀን ሰልፍ በረታ፤ የእስራኤልም ንጉሥ በሶርያውያን ፊት እስከ ማታ ድረስ በሰረገላው ላይ ራሱን ይደግፍ ነበር፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ሞተ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 18:34
8 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሁሉ ጠባቂ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው በጎች በተ​ራ​ሮች ላይ ተበ​ት​ነው አየሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ለእ​ነ​ዚህ ጌታ የላ​ቸ​ውም፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በሰ​ላም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ አለ” ብሎ ተና​ገረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ወጥቶ በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ይወ​ድቅ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ አክ​ዓ​ብን የሚ​ያ​ታ​ልል ማን ነው?” አለ። አን​ዱም እን​ደ​ዚህ፥ ሌላ​ውም እን​ደ​ዚያ ያለ ነገር ተና​ገረ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “በደ​ኅና ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ አል​ተ​ና​ገ​ረም” አለ። “ደግ​ሞም እና​ንተ ሕዝቡ ሁሉ ስሙኝ” አለ።


አንድ ሰውም ቀስ​ቱን በድ​ን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በጥ​ሩሩ መጋ​ጠ​ሚያ በኩል ሳን​ባ​ውን ወጋው። ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና እጅ​ህን ግታ፤ ከጦ​ር​ነት ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ ቤቱ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በሰ​ላም ተመ​ለሰ።


በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።