2 ዜና መዋዕል 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሠራዊቱን አኖረ፤ በይሁዳም ሀገር፥ አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች መሳፍንቱን አስቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ፤ እንዲሁም በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም መንደሮች ዘበኞች አስቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፥ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችና በየገጠሩ ሁሉ እንዲሁም አባቱ ንጉሥ አሳ ድል አድርጎ በያዛቸው በኤፍሬም ግዛት ባሉት ከተሞች ሁሉ ወታደሮቹን አሰፈረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፤ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ። |
አብያም ኢዮርብዓምን ተከትሎ አሳደደው፤ ከእርሱም ከተሞቹን ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሳናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ።
አሳም ይህን ቃልና የነቢዩን የአዳድን ልጅ የአዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ ጸና፤ ከይሁዳና ከብንያምም ሀገር ሁሉ በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከያዛቸው ከተሞች ርኵሰትን ሁሉ አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ፊት የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አደሰ።
እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊተኛዪቱም በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና፥ ጣዖትንም አልፈለገምና፤