እነዚህ ሁሉ የይዴኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
2 ዜና መዋዕል 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳም ከተሞች ብዙ ሥራ ሠራ፤ በኢየሩሳሌምም ጽኑዓን ኀያላን ሰልፈኞች ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳም ከተሞች እጅግ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ነበረው። ደግሞም በቂ ልምድ ያላቸውን ተዋጊዎች በኢየሩሳሌም አስቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳም ከተሞች ብዙ ሥራ ሠራ፥ በኢየሩሳሌምም ጽኑዓን ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳም ከተሞች ብዙ ሥራ ሠራ፤ በኢየሩሳሌምም ጽኑዓን ኃያላን ሰልፈኞች ነበሩት። |
እነዚህ ሁሉ የይዴኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
እርሱም የይሁዳን ሰዎች፥ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ቅጥርም፥ ግንብም፥ መዝጊያም፥ መወርወሪያም እናድርግባቸው፤ ምድሪቱንም እንገዛታለን፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደ ፈለግነው እርሱም ይፈልገናልና፤ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል፤ ሁሉንም አከናወነልን” አለ።
ቍጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድናስ፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ፤