Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ቍጥ​ራ​ቸ​ውም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ሻለ​ቆች አለ​ቃው ዓድ​ናስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋራ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ቁጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከይሁዳ ነገድ ለተመለመሉት ወታደሮች አዛዥ ዐድና ተብሎ የሚጠራ የጦር መኰንን ነበር፤ በእርሱም ሥር ሦስት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ቍጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 17:14
11 Referencias Cruzadas  

ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል።


ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው።


ሮብ​ዓ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ቤት የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞች ጐል​ማ​ሶ​ችን ሰበ​ሰበ።


አብ​ያም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አራት መቶ ሺህ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ይዞ በእ​ርሱ ላይ ተሰ​ለፈ።


ለአ​ሳም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚ​ሸ​ከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይ​ሁዳ ሠራ​ዊት፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ፥ ቀስ​ትም የሚ​ገ​ትሩ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ የብ​ን​ያም ሰዎች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ብዙ ሥራ ሠራ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ነበ​ሩት።


ከእ​ር​ሱም በኋላ አለ​ቃው ኢዮ​አ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ሠራ​ዊት ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ንጉ​ሡን በጠ​ላቱ ላይ የሚ​ያ​ግዙ፥ በታ​ላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ነበሩ።


በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ወንድ ሁሉ በየ​ራሱ፥ በየ​ወ​ገ​ኑም፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ተና​ገሩ።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ድምር፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ ወን​ዱን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ቍጠሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos