2 ዜና መዋዕል 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳም በነገሠበት ዘመን እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ጦርነት አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ሠላሳ ዐምስተኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ምንም ዐይነት ጦርነት አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳም እስከ ነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ጦርነት አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳ እስከ ነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ በአገሪቱ ላይ ጦርነት አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳም እስከ ነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ሰልፍ አልነበረም። |
በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በእስራኤል ሁሉ ላይ በቴርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ።
አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ እርሱም የቀደሰውን ወርቁንና ብሩን፥ ልዩ ልዩውንም ዕቃ ወደ እግዚአብሔር ቤትአገባ።
አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘመተ፥ ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ አሳ ማንም መውጣትና መግባት እንዳይችል ራማን ሠራት።
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”