ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በድንኳኑ አጠገብ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጣ፤ በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
2 ዜና መዋዕል 15:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬዎችንና ሰባት ሺህ በጎችን ለእግዚአብሔር ሠዋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለእግዚአብሔር ሠዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎች ለጌታ ሠዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ይዘው ካመጡት ምርኮም በዚያን ቀን ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎች ለእግዚአብሔር ሠዉ። |
ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በድንኳኑ አጠገብ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጣ፤ በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
በዚያችም ዕለት ንጉሡ ሰሎሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችንና መቶ ሃያ ሺህ በጎችን ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቅዳሴ አከበሩ።
ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት።
ሳኦልም፦“ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ ከበጎችና ከላሞች መንጋዎች መልካም መልካሙን አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አመጣን፤ የቀሩትንም ፈጽሜ አጠፋሁ” አለው።
ሕዝቡ ግን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በጌልጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችና በሬዎች ከምርኮው ወሰዱ” አለው።