2 ዜና መዋዕል 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልከውም ጠሩት፤ ኢዮርብዓምና እስራኤልም ሁሉ ወደ ሮብዓም መጥተው እንዲህ አሉት፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮርብዓምንም ልከው አስጠሩት፤ ከዚያም እርሱና እስራኤል ሁሉ ወደ ሮብዓም ሄደው እንዲህ አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልከውም ጠሩት፤ ኢዮርብዓምና እስራኤልም ሁሉ መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት የሚኖሩ ነገዶች መልእክት ልከው አስጠሩት፤ ከእርሱም ጋር አብረው ወደ ሮብዓም በመቅረብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልከውም ጠሩት፤ ኢዮርብዓምና እስራኤልም ሁሉ መጥተው ሮብዓምን |
የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮርብዓም ከግብፅ ተመለሰ።
“አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቅልልልን፥ እኛም እንገዛልሃለን።”