በእጆችሽም የንጹሓን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በጕድጓድ ፈልጌ አላገኘሁትም።
1 ጢሞቴዎስ 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንዳንዶች ሰዎች ኀጢአት የተገለጠ ነው፤ ፍርድንም ያመለክታል፤ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአንዳንድ ሰዎች ኀጢአት ግልጽ ነው፤ ከእነርሱም ቀድሞ ፍርድ ቦታ ይደርሳል፤ ሌሎችን ግን ኀጢአታቸው ይከተላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ በመሆኑ አስቀድሞ ፍርድን ያመለክታል፤ የሌሎች ግን የሚገለጠው ዘግየት ብሎ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት ግልጥ በመሆኑ አስቀድሞ ፍርዱን ያመለክታል፤ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት ግን የሚገለጠው ዘግየት ብሎ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአንዳንዶች ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ ነው ፍርድንም ያመለክታል፥ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤ |
በእጆችሽም የንጹሓን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በጕድጓድ ፈልጌ አላገኘሁትም።
የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ሐሰተናነት ለክብሩ ከፍ ከአለ እንግዲህ እኔን እንደ ኀጢአተና ለምን ይፈርድብናል?
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፡ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል፤” ይላል።