1 ጢሞቴዎስ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፤ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፤ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ የተፈጠረ አዳም ነው፤ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። |
እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።”
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”