ከወንድሞች ሁሉ ጋር በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።
የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው።
ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ መሳሳም ሰላም በሉአቸው።
ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ ሰላምታ ሰላም ተባባሉ፤ የክርስቶስ ማኅበረ ክርስቲያንም ሰላም ይሉአችኋል።
ወንድሞቻችሁ ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ በተቀደሰች ሰላምታ እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ።