“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
1 ሳሙኤል 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ መሴፋ ምድርም በደረሱ ጊዜ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፥ “አባቴ ስለ አህዮች ማሰብን ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፤ እንመለስ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ጹፍ ግዛት በደረሱ ጊዜ ሳኦል ዐብሮት የነበረውን አገልጋይ፣ “አባቴ ይህን ጊዜ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ስለሚጀምር፣ ና እንመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጹፍ ምድር በደረሱ ጊዜ ሳኦል አብሮት የነበረውን አገልጋይ፥ “አባቴ ይህን ጊዜ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ስለሚጀምር፥ ና እንመለስ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ጹፍ ምድር በደረሱ ጊዜ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን አገልጋይ፦ “ከእንግዲህ ወዲህ አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡ ቀርቶ ስለ እኛ መጨነቅ ስለሚጀምር አሁንስ ወደ ቤት እንመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜም ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፦ አባቴ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፥ እንመለስ አለው። |
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ወደ አደባባይ ወደ ሹሞቹና ወደ ነገሥታቱ፥ ወደ መኳንንቱም በሚወስዱአችሁ ጊዜ የምትሉትንና የምትናገሩትን አታስቡ።
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።
በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የናሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤልዩ ልጅ ፥ የኢያርምያል ልጅ፥ ኤፍራታዊው ሕልቃና ነበረ።
ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ግዛት በቤቴል አውራጃ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች እየቸኰሉ ሲሄዱ ታገኛለህ፤ እነርሱም፦ ልትፈልጉአቸው ሂዳችሁ የነበራችሁላቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል።