በፊቱም ከአለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው፤ የብንያምም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ። እነርሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው።
1 ሳሙኤል 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፥ “በአንተ ዘንድ አኑረው ብዬ የሰጠሁህን እድል ፋንታ አምጣ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፣ “ለይተህ አስቀምጥ ብዬ የሰጠሁህን የሥጋ ብልት አምጣው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፥ “ለይተህ አስቀምጥ ብዬ የሰጠሁህን የሥጋ ብልት አምጣው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም የወጥ ቤቱን ሠራተኛ ጠርቶ “ለብቻው አስቀምጥ ብዬ የሰጠሁህን ብልት ሥጋ አምጣ” አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ወጥቤቱን፦ በአንተ ዘንድ አኑረው ብዬ የሰጠሁህን እድል ፈንታ አምጣ አለው። |
በፊቱም ከአለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው፤ የብንያምም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ። እነርሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው።
ለሐናም ልጅ ስላልነበራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕልቃናም ከዚያችኛይቱ ይልቅ ሐናን ይወድድ ነበር። እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበር።
ሳሙኤልም ሳኦልንና ብላቴናውን ወስዶ ወደ አዳራሽ አገባቸው፥ ሰባ ሰዎችም ምሳ በሚበሉበት በምርፋቁ ራስ አስቀመጣቸው፤
ወጥቤቱም ወርቹን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፥ “ሳኦልን ለምስክር ከባልንጀራህ ተለይቶ ቀርቦልሃልና እነሆ፥ በልተህ የተረፈህን በፊትህ አኑር” አለው። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።