La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ካህ​ና​ት​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ጠር​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ላይ ምን እና​ድ​ርግ? ወደ ስፍ​ራ​ዋስ በምን እን​ስ​ደ​ዳት? አስ​ታ​ው​ቁን” አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የጌታን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቡ ካህናታቸውንና አስማተኞቻቸውን ጠርተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁአቸው፤ “ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ምን ማድረግ የሚሻለን ይመስላችኋል? ወደ ስፍራው እንዲመለስ ብናደርግ በምን ሁኔታ እንላከው? ዘዴውን ንገሩን” አሉአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠርተው፥ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራውስ በምን እንስደደው? አስታውቁን አሉ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 6:2
10 Referencias Cruzadas  

በነ​ጋም ጊዜ መን​ፈሱ ታወ​ከ​ች​በት፤ የግ​ብፅ ሕልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ች​ንና ጠቢ​ባ​ንን ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም ሕል​ሙን ነገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ ለፈ​ር​ዖን ሕል​ሙን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ለት አል​ተ​ገ​ኘም።


ፈር​ዖ​ንም ጠቢ​ባ​ን​ንና መተ​ተ​ኞ​ችን ጠራ፤ የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ ደግሞ አደ​ረጉ።


ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።


ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ወደ እነ​ርሱ ሰበ​ሰ​ቡና፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ምን እና​ድ​ርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎ​ችም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦ​ትም ወደ ጌት ሄደች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሰባት ወር ተቀ​መ​ጠች። ምድ​ራ​ቸ​ውም አይ​ጦ​ችን አወ​ጣች።