ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
1 ሳሙኤል 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤትሳሚስ ሰዎችም በእርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይናቸውንም ከፍ አድርገው የእግዚአብሔርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎአቸውም ተቀበሉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የቤትሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤትሼሜሽም ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው በተመለከቱም ጊዜ ታቦቱን አዩ፤ ያንንም በማየታቸው እጅግ ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤትሳሚስ ሰዎችም በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፥ ዓይናቸውንም ከፍ አድርገው ታቦቱን አዩ፥ በማየታቸውም ደስ አላቸው። |
ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው “እምቧ” እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆችም እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።
ሰረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኦሴዕ እርሻ መጣ፤ ታላቅም ድንጋይ በነበረበት በዚያ ቆመ፤ የሰረገላውንም ዕንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።