ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
1 ሳሙኤል 27:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኰበለለ ነገሩት፤ ከዚያም በኋላ ደግሞ አልፈለገውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ ዳዊት ወደ ጋት እንደ ሸሸ በሰማ ጊዜ፣ እርሱን ማሳደዱን ተወ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ ዳዊት ወደ ጋት እንደ ሸሸ በሰማ ጊዜ፥ እርሱን ማሳደዱን ተወ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ዳዊት ወደ ጋት ሸሽቶ መሄዱን በሰማ ጊዜ እርሱን ፈልጎ ለማግኘት ያደርገው የነበረውን ሙከራ ሁሉ አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኮበለለ ሰማ፥ ከዚያም በኋላ ደግሞ አልፈለገውም። |
ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፤ እነሆ፥ ስንፍና እንደ አደረግሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወቅሁ” አለ።
ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።
ዳዊትም አንኩስን፥ “አገልጋይህ በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ በዚህ ሀገር ከከተሞችህ በአንዲቱ የምቀመጥበት ስፍራ ስጠኝ፤ ስለ ምን እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋር በንጉሥ ከተማ እቀመጣለሁ?” አለው።።