Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አገ​ል​ጋ​ይህ በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ በዚህ ሀገር ከከ​ተ​ሞ​ችህ በአ​ን​ዲቱ የም​ቀ​መ​ጥ​በት ስፍራ ስጠኝ፤ ስለ ምን እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከአ​ንተ ጋር በን​ጉሥ ከተማ እቀ​መ​ጣ​ለሁ?” አለው።።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም ዳዊት አንኩስን፣ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ እኖር ዘንድ ስፍራ ይሰጠኝ፤ ስለ ምን አገልጋይህ ካንተ ጋራ በንጉሥ ከተማ ይቀመጣል?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከዚያም ዳዊት አኪሽን፥ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፥ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ እኖር ዘንድ ስፍራ ይሰጠኝ፤ ስለምን አገልጋይህ ካንተ ጋር በንጉሥ ከተማ ይቀመጣል?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዳዊትም ንጉሥ አኪሽን “የምትወደኝ ከሆንክ በአንድ ትንሽ ከተማ እንድኖር ፍቀድልኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ በመናገሻ ከተማ ከአንተ ጋር መኖር አይገባኝም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም አንኩስን፦ በዓይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ በዚህ አገር በአንዲቱ ከተማ የምቀመጥበት ስፍራ ስጠኝ፥ ስለ ምን እኔ ባሪያህ ከአንተ ጋር በንጉሥ ከተማ እቀመጣለሁ? አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 27:5
4 Referencias Cruzadas  

በግ ጠባቂ ሁሉ ለግ​ብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም እን​ድ​ት​ቀ​መጡ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ታ​ችን ጀም​ረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እን​ስሳ አር​ቢ​ዎች ነን” በሉት።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኰበ​ለለ ነገ​ሩት፤ ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ አል​ፈ​ለ​ገ​ውም።


በዚ​ያም ቀን አን​ኩስ ሴቄ​ላ​ቅን ሰጠው፤ ስለ​ዚ​ህም ሴቄ​ላቅ እስከ ዛሬ ድረስ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ሆነች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos