1 ሳሙኤል 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሕዝቡንና የኔር ልጅ አቤኔርን ጠራቸው፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስምን?” አለው። አቤኔርም መልሶ፥ “አንተ የምትጠራኝ ማን ነህ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ሰራዊቱንና የኔርን ልጅ አብኔርን፣ “አበኔር ሆይ፣ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አበኔርም፣ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሠራዊቱንና የኔርን ልጅ አቤኔርን፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አቤኔርም፥ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድምፁንም ከፍ አድርጎ ወደ ሳኦል ወታደሮችና ወደ አበኔር በመጮኽ “አበኔር ሆይ! መልስ ስጠኝ” አለው። አበኔርም “እንዲህ እያልክ በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለሕዝቡና ለኔር ልጅ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን? ብሎ ጮኸ። አበኔርም መልሶ፦ ለንጉሡ የምትጮኸው አንተ ማን ነህ? አለ። |
የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ።
ዳዊትም አቤኔርን፥ “አንተ ጐልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለምን ነው?