ይህንም ነገር ለኢዮአታም በነገሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድምፁንም አንሥቶ አለቀሰ፤ እንዲህም አላቸው፥ “የሰቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግዚአብሔርም ይስማችሁ።
1 ሳሙኤል 26:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ማዶ ተሻገረ፤ በተራራውም ራስ ላይ ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ርቀት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዳዊት ወደ ማዶ ተሻግሮ በኰረብታው ጫፍ ላይ ራቅ ብሎ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ርቀት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዳዊት ወደ ማዶ ተሻግሮ በኰረብታው ጫፍ ላይ ራቅ ብሎ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ርቀት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት ከሸለቆው ባሻገር ወደሚገኘው ቦታ ተሻገረ፤ ከእነርሱም ራቅ ብሎ በተራራው ጫፍ ላይ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደዚያ ተሻገረ፥ በተራራውም ራስ ላይ ርቆ ቆመ፥ በመካከላቸውም ሰፊ ስፍራ ነበረ። |
ይህንም ነገር ለኢዮአታም በነገሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድምፁንም አንሥቶ አለቀሰ፤ እንዲህም አላቸው፥ “የሰቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግዚአብሔርም ይስማችሁ።
ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።
ዳዊትም በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፤ ወደ ቤታቸውም ተመለሱ። ማንም ያየ አልነበረም፤ ያወቃቸውም ማንም አልነበረም፤ የነቃም ማንም አልነበረም፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር።
ዳዊትም ሕዝቡንና የኔር ልጅ አቤኔርን ጠራቸው፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስምን?” አለው። አቤኔርም መልሶ፥ “አንተ የምትጠራኝ ማን ነህ?” አለ።