ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቤግያ ጋር ወደዚያ ወደ ኬብሮን ወጣ።
1 ሳሙኤል 25:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤግያም ፈጥና ተነሣች፤ በአህያም ላይ ተቀመጠች፤ አምስቱም ገረዶችዋ ተከተሉአት፤ የዳዊትንም መልእክተኞች ተከትላ ሄደች፤ ሚስትም ሆነችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢግያም ወዲያውኑ በአህያ ላይ ተቀምጣ ዐምስት አገልጋዮቿን በማስከተል፣ ከዳዊት መልእክተኞች ጋራ ሄደች፤ ለዳዊትም ሚስት ሆነችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢግያም ወዲያውኑ በአህያ ላይ ተቀምጣ አምስት አገልጋዮቿን በማስከተል፥ ከዳዊት መልእክተኞች ጋር ሄደች፤ ለዳዊትም ሚስት ሆነችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈጥናም ተነሥታ በአህያዋ ላይ ተቀመጠች፤ በአምስት ገረዶችዋም ታጅባ ከዳዊት አገልጋዮች ጋር በመሄድ ሚስቱ ሆነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢግያም ፈጥና ተነሣች፥ በአህያም ላይ ተቀመጠች፥ አምስቱም ገረዶችዋ ተከተሉአት፥ የዳዊትንም መልእክተኞች ተከትላ ሄደች፥ ሚስትም ሆነችው። |
ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቤግያ ጋር ወደዚያ ወደ ኬብሮን ወጣ።
ለዳዊትም ወንዶች ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፤ በኵሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ።
ሁለተኛውም ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቤግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌድሶር ንጉሥ ከቶልሜልም ልጅ ከመዓክ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።
ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።
የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቤግያ ተማርከው ነበር።