ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
1 ሳሙኤል 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ወደ ቂአላ ወርደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ይከብቡ ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ፣ ሰራዊቱን በሙሉ ለጦርነት ጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ብሎም ሳኦል ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ ሠራዊቱን በሙሉ ለጦርነት ጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሳኦል ወታደሮቹን ለጦርነት ጠርቶ ወደ ቀዒላ በመዝመት ዳዊትንና ተከታዮቹን እንዲከቡ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ይከብቡ ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። |
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
ዳዊትም፥ “የእስራኤል አምላክ አቤቱ! በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ።
ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነገረው፤ ሳኦልም፥ “መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል” አለ።
ዳዊትም ሳኦል በእርሱ ለክፋት ዝም እንደማይል ዐወቀ፤ ዳዊትም ካህኑን አብያታርን፥ “የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣ” አለው።