La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 23:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም ሊፈ​ል​ጉት ሄዱ፤ ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እር​ሱም በማ​ዖን ምድረ በዳ ወዳ​ለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦ​ልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊ​ትን በማ​ዖን ምድረ በዳ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደ ሰማ፣ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደሰማ፥ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልና ወታደሮቹም ዳዊትን ለማሳደድ ወጥተው ሄዱ፤ ዳዊትም ይህን ስላወቀ በማዖን ምድረ በዳ አለት ወደበዛበት አንድ ኮረብታ አልፎ በዚያ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ ዳዊትን የመከታተል ተግባሩን ቀጠለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልና ሰዎቹም ሊፈልጉት ሄዱ፥ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ዓለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ፥ ሳኦልም ያንን በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 23:25
5 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለቴ፥ አም​ባ​ዬም፥ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነው፤


ሶም​ሶ​ንም ጭን ጭና​ቸ​ውን ብሎ በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል መታ​ቸው፤ ወር​ዶም ኢጣም በም​ት​ባል ዋሻ በወ​ንዝ ዳር ተቀ​መጠ።


የዚፍ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከሳ​ኦል በፊት ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ግን በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በኩል በዓ​ረባ በማ​ዖን ምድረ በዳ ነበሩ።


ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በአ​ንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በሌ​ላው ወገን ሄዱ። ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ያመ​ልጥ ዘንድ ተሰ​ውሮ ነበር። ሳኦ​ልና ሰዎቹ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹን ለመ​ያዝ ከብ​በ​ዋ​ቸው ነበ​ርና።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ማሳ​ደ​ድን ትቶ ተመ​ለሰ። ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመ​ለ​ያ​የት ዓለት ተባለ።