የኢያቡስቴንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሡንም፥ “ነፍስህን ይሻ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ እነሆ፤ እግዚአብሔርም ዛሬ ከጠላትህ ከሳኦልና ከዘሩ ለጌታችን ለንጉሥ በቀሉን መለሰለት” አሉት።
1 ሳሙኤል 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሳኦል ሊፈልገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአውክሞዲስ ውስጥ ይኖር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ሳለ፣ ሳኦል ሊገድለው መምጣቱን አየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ሳለ፥ ሳኦል ሊገድለው መምጣቱን አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ሳኦል ሊገድለው መምጣቱን ተመለከተ። ዳዊት በዚፍ አጠገብ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሖሬሽ ይገኝ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሳኦል ነፍሱን ሊፈልግ እንደ ወጣ አየ፥ ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ በጥሻው ውስጥ ይኖር ነበር። |
የኢያቡስቴንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሡንም፥ “ነፍስህን ይሻ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ እነሆ፤ እግዚአብሔርም ዛሬ ከጠላትህ ከሳኦልና ከዘሩ ለጌታችን ለንጉሥ በቀሉን መለሰለት” አሉት።
ዳዊትም በምድረ በዳ በጠባቡ በማሴሬም ይኖር ነበር፥ በአውክሞዲስ ውስጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም።
የዳዊትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፤ ይልቁንስ ፍልስጥኤማውያንን ለመዝረፍ ወደ ቂአላ ብንሄድ እንዴት እንሆናለን?” አሉት።
ሳኦልም በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ በመንገዱ አጠገብ ሰፈረ። ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፥ ዳዊትም ሳኦል ሊፈልገው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ ዐወቀ።