1 ሳሙኤል 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም የዮናታንን ቃል ሰማ፤ ሳኦልም፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም” ብሎ ማለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም ዮናታንን ካዳመጠው በኋላ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም” ብሎ ማለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም ዮናታንን ካዳመጠው በኋላ፥ “በሕያው ጌታ እምላለሁ! ዳዊት አይገደልም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ዮናታን የተናገረውን ቃል በመስማት ዳዊትን እንደማይገድለው የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ በመማል አረጋገጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም የዮናታንን ቃል ሰማ፥ ሳኦልም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም ብሎ ማለ። |
እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኀጢኣቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል” አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”