ዳዊትም፥ “ይሁን፤ በመልካም ፈቃደኛነት ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፤ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም” አለው።
1 ሳሙኤል 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን ጠበቀው፤ በነጋው እንዲገድሉት መልእክተኞቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስቱም ሜልኮል፥ “በዚህች ሌሊት ነፍስህን ካላዳንህ ነገ ትገደላለህ” ብላ ነገረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም የዳዊትን ቤት ከብበው በማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮል ግን፣ “ሕይወትህን ለማትረፍ በዚህች ሌሊት ካልሸሸህ፣ በነገው ቀን ትገደላለህ” ብላ አስጠነቀቀችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም የዳዊትን ቤት ከበው በማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮል ግን፥ “ሕይወትህን ለማትረፍ በዚህች ሌሊት ካልሸሸህ፥ በነገው ቀን ትገደላለህ” ብላ አስጠነቀቀችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ምሽት ሳኦል የዳዊትን ቤት ከበው ማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ፤ የዳዊት ሚስት ሜልኮል “ዛሬ ማታ ነፍስህን ካላዳንህ በቀር ነገ ጧት ትገደላለህ” ስትል አስጠነቀቀችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትን ጠብቀው በነጋው እንዲገድሉት መልእክተኞቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፥ ሚስቱም ሜልኮል፦ በዚህች ሌሊት ነፍስህን ካላዳንህ ነገ ትገደላለህ ብላ ነገረችው። |
ዳዊትም፥ “ይሁን፤ በመልካም ፈቃደኛነት ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፤ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም” አለው።
ለጋዛ ሰዎችም፥ “ሶምሶን ወደዚህ መጥቶአል” ብለው ነገሩአቸው፤ ከበቡትም። ሌሊቱንም ሁሉ በከተማዪቱ በር ሸመቁበት፥ “ማለዳ እንገድለዋለን” ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ።
ሳኦልም ዳዊትን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ የነቢያትንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙኤልም አለቃቸው ሆኖ በመካከላቸው ቆሞ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በሳኦል መልእክተኞች ላይ ወረደ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገሩ ጀመር።
የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ መንግሥትህ አትጸናም፤ አሁንም ሞት የሚገባው ነውና ያን ብላቴና ያመጡት ዘንድ ላክ” አለው።