እነርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁላችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራዊት ስለሆንህ ብንሸሽ ልባቸው አይከተለንምና፥ እኩሌታችንም ብንሞት ልባቸው አይከተለንምና አትውጣ፤ አሁንም መርዳትን ትረዳን ዘንድ በከተማ ብትኖርልን ይሻለናል” አሉት።
1 ሳሙኤል 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶችም፥ “ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊትም ዐሥር ሺህ ገደለ” እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቶቹም እንዲህ ሲሉ በመቀባበል ዘፈኑ፤ “ሳኦል ሺሕ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺሕ ገደለ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶችም “ሳኦል ሺ ገዳይ! ዳዊት ዐሥር ሺ ገዳይ!” እያሉ በቅብብል ይዘፍኑ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶቹም ባደረጉት የአቀባበል ሥርዓት ላይ “ሳኦል ሺህ ገዳይ! ዳዊት ግን ዐሥር ሺህ ገዳይ!” እያሉ ዘፈኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቶችም፦ ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር። |
እነርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁላችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራዊት ስለሆንህ ብንሸሽ ልባቸው አይከተለንምና፥ እኩሌታችንም ብንሞት ልባቸው አይከተለንምና አትውጣ፤ አሁንም መርዳትን ትረዳን ዘንድ በከተማ ብትኖርልን ይሻለናል” አሉት።
የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ የቀባው፥ የታማኙ ሰው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የታማኙ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር ይህ ነው፤
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ማርያምም አስቀድማ ለእግዚአብሔር እንዘምር አለች፥ “ለእግዚአብሔር እንዘምር በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጥሎአልና።”
የአንኩስ ብላቴኖችም፥ “ይህ ዳዊት የሀገሩ ንጉሥ አይደለምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘፈን የዘመሩለት እርሱ አይደለምን?” አሉት።