የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች ደስ እንዳይላቸው፥ የቈላፋንም ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ።
1 ሳሙኤል 18:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ፥ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ዳዊትን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ከገደለ በኋላ፣ ሰዎቹ ወደ የቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ፣ ሴቶች ከበሮና መሰንቆ ይዘው እየዘፈኑ፣ እየጨፈሩና እልል እያሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ከገደለ በኋላ፥ ሰዎቹ ወደየቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ፥ ሴቶች ከበሮና መሰንቆ ይዘው እየዘፈኑ፥ እየጨፈሩና እልል እያሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ሲመለስና ወታደሮችም ወደየቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ፥ በእስራኤል በሚገኙት ከተሞች ሁሉ የሚኖሩ ሴቶች ሳኦልን ለመቀበል ወጡ፤ እነርሱም በእልልታ እየዘፈኑና እየጨፈሩ፥ የመስንቆ ድምፅ እያሰሙ አታሞ ይመቱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ንጉሡን ሳኦልን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ። |
የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች ደስ እንዳይላቸው፥ የቈላፋንም ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ።
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ማርያምም አስቀድማ ለእግዚአብሔር እንዘምር አለች፥ “ለእግዚአብሔር እንዘምር በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጥሎአልና።”
እግዚአብሔር በላዩ የሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።
ዮፍታሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትቀበለው ወጣች፤ ለእርሱም የሚወድዳት አንዲት ብቻ ነበረች። ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም።
ዳዊትም ሳኦል ወደ ላከው ሁሉ ይሄድ ነበር፤ አስተውሎም ያደርግ ነበር፤ ሳኦልም በጦረኞች ላይ ሾመው፤ ይህም በሕዝብ ሁሉ ዐይንና በሳኦል ባሪያዎች ዐይን መልካም ነበረ።