እነርሱም አሉት፥ “እኛ የጠላንህ አይደለም፤ በመልካም አኑረን፥ በመልካም አሰናበትንህ እንጂ፥ አሁንም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቡሩክ ነህ።
1 ሳሙኤል 18:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፤ እስራኤልም ሁሉ ወደዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ እንደ ሆነና ልጁ ሜልኮልም እንደ ወደደችው በተረዳ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል፥ ጌታ ከዳዊት ጋር እንደ ሆነና ልጁ ሜልኮልም እንደወደደችው በተረዳ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር መሆኑንና ልጁም ሜልኮል እርሱን እንደ ወደደችው አረጋገጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፥ እስራኤልም ሁሉ ወደዱት። |
እነርሱም አሉት፥ “እኛ የጠላንህ አይደለም፤ በመልካም አኑረን፥ በመልካም አሰናበትንህ እንጂ፥ አሁንም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቡሩክ ነህ።
ላባም፥ “በዐይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና።
ጌታውም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
ዳዊትና ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ሁለት መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ ዳዊትም ለንጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለባቸውን አምጥቶ በቍጥራቸው ልክ ለንጉሡ ሰጠ። ሳኦልም ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።
ጠላቱን ተቸግሮ አግኝቶ በመልካም መንገድ ሸኝቶ የሚሰድድ ማን ነው? ስለዚህ ለእኔ ስላደረግኸው ቸርነት እግዚአብሔር መልካሙን ይመልስልህ።
ሳኦልም ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድረግን ታደርጋለህ፤ መቻልንም ትችላለህ” አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።