በዚያም ቀን ሳኦል ወሰደው፤ ወደ አባቱም ቤት ይመልሰው ዘንድ አልፈቀደለትም።
ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን ዐብሮት እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም።
ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን አብሮት እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊትን ከእርሱ ጋር እንዲኖር አደረገ፤ ወደ ቤቱም እንዲሄድ አላሰናበተውም፤
በዚያም ቀን ሳኦል ወሰደው፥ ወደ አባቱም ቤት ይመልሰው ዘንድ አልተወውም።
ዳዊትም የአባቱን በጎች ለመጠበቅ ከሳኦል ዘንድ ወደ ቤተ ልሔም ይመላለስ ነበር።
ዮናታንም ዳዊትን ጠርቶ ይህን ነገር ሁሉ ነገረው፤ ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፤ እንደ ቀድሞውም በፊቱ ነበረ።