ሳኦልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው።
ሳኦልም፣ ዳዊት እንደ ተሳካለት ባየ ጊዜ ፈራው፤
ሳኦልም፥ ዳዊት እንደ ተሳካለት ባየ ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፈራው፤
ሳኦልም የዳዊትን ተልእኮ መሳካት እየተመለከተ በይበልጥ ይፈራው ጀመር፤
ሳኦልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው።
እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በልዕልና የሚኖር።
ዘመኑን እየዋጃችሁ ከሃይማኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማስተዋል ሂዱ።
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ፥ ከሳኦልም ስለ ተለየ ሳኦል ከዳዊት ፊት የተነሣ ፈራ።
ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ ብልህና ዐዋቂ ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።
ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱ።