የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
1 ሳሙኤል 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ ብልህና ዐዋቂ ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበር የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ከእርሱ ጋር ስለ ነበር የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ። |
የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
በዚያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍሮችን አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ያድነው ነበር።
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮችን አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ያድነው ነበር።
እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊተኛዪቱም በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና፥ ጣዖትንም አልፈለገምና፤
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ፤ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም።
ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፤ ሰውየውም ጠቢብ፥ ተዋጊም ነው፤ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለ።