1 ሳሙኤል 15:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም እስከ ሞተበት ቀን ድረስ ሳኦልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም፤ ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል ለሳኦል ቢያለቅስለትም እንኳ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ዳግመኛ ሊያየው አልሄደም፤ እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጸተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል ለሳኦል ቢያለቅስለትም እንኳ እስከሞተበት ዕለት ድረስ ዳግመኛ ሊያየው አልሄደም፤ ጌታም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጸተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ሳሙኤል በነበረበት ጊዜ ሁሉ ንጉሥ ሳኦልን በዐይኑ አላየውም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጽቶ ስለ ነበር፥ ለእርሱ በማዘን ያለቅስለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳሙኤልም እስከ ሞተበት ቀን ድረስ ሳኦልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም፥ ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ። |
ዘወትር እንደምነግራችሁ፥ ልዩ አካሄድ የሚሄዱ ብዙዎች አሉና፤ አሁንም እነርሱ የክርስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች እንደ ሆኑ በግልጥ እያለቀስሁ እነግራችኋለሁ።
“ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ።” ሳሙኤልም አዘነ። ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።
ልብሱንም አወለቀ፤ በፊታቸውም ትንቢት ተናገረ፤ ራቁቱንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚያም ሌሊት ሁሉ ተጋደመ። ስለዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነቢያት መካከል ነውን?” ይባባሉ ነበር።