1 ሳሙኤል 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “በዐይንህ ፊት ታናሽ የነበርህ ብትሆንም፣ የእስራኤል ነገዶች መሪ ሆነህ የለምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ስለ ራስህ የነበረህ ግምት ታናሽ የነበር ቢሆንም፥ የእስራኤል ነገዶች መሪ አልሆንክምን? ጌታም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ስለ ራስህ የነበረህ ግምት አነስተኛ ቢሆንም የእስራኤል ነገዶች መሪ አልሆንክምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም አለ፦ በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ። |
እርሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ በምናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂቶች ናቸው፤ እኔም በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።
ሳሙኤልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል” ብሎ መለሰ።
ሳኦልም መልሶ፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ ሰው አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ?” አለ።