የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ።
1 ሳሙኤል 14:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም አባት ቂስ ነበረ፤ የአቤኔርም አባት የአብኤል ልጅ የያሚን ልጅ ኔር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር ሁለቱም የአቢኤል ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር የአቢኤል ልጆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር የአቢኤል ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም አባት ቂስ ነበረ፥ የአበኔርም አባት ኔር የአቢኤል ልጅ ነበረ። |
የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ።
ዳዊትም በቀስታ ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦልም በድንኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።
ከብንያም ልጆች ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአብሔል ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥ የባሔር ልጅ፥ የብንያም ሰው፥ የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።
ሳኦልም መልሶ፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ ሰው አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ?” አለ።