ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው።
1 ሳሙኤል 14:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ዮናታንም፥ “በእጄ ባለው በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በርግጥ ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ እሞታለሁ” ብሎ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፣ “እስኪ ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፣ “በዘንጌ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆ፤ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ነገር ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሳኦል ዮናታንን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። ዮናታንም “በበትሬ ጫፍ አስነክቼ ጥቂት ማር. ቀምሻለሁ እነሆ በዚህ እገኛለሁ፤ ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዮናታንን፦ ያደረግኸውን ንገረኝ አለው፥ ዮናታንም፦ በእጄ ባለው በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በእርግጥ ቀምሻለሁ፥ እነሆኝ፥ እሞታለሁ ብሎ ነገረው። |
ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው።
ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ባማለ ጊዜ አልሰማም ነበር፤ እርሱም በእጁ ያለችውን በትር አንሥቶ ጫፍዋን ወደ ወለላው ነከረ፤ እጁንም ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ።
ሳኦልም፥ “በእኔና በዮናታን መካከል ዕጣ አጣጥሉን፤ እግዚአብሔር ዕጣ ያወጣበትም ይሞታል” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም” አሉት፤ ሳኦልም ሕዝቡን እንቢ አላቸው። በእርሱና በልጁ በዮናታን መካከልም ዕጣ አጣጣሉ። ዕጣውም በልጁ በዮናታን ላይ ወጣ።