La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሕ​ዝ​ቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባ​ትህ፦ ዛሬ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝ​ቡን መሐላ አም​ሎ​አ​ቸ​ዋል” አለው፤ ሕዝ​ቡም ደከሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አንዱ ወታደር፣ “አባትህ ሰራዊቱን፣ ‘ዛሬ እህል የሚቀምስ ማንኛውም ሰው የተረገመ ይሁን!’ በማለት በጽኑ መሐላ አስሯል። ሰው ሁሉ የተዳከመው በዚሁ ምክንያት ነው” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሕዝቡም አንድ ሰው፥ “አባትህ ሕዝቡን፥ ‘ዛሬ እህል የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!’ በማለት በጽኑ መሓላ አስጠንቅቆናል” አለው። ሰው ሁሉ ተዳክሞ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ “እኛ ሁላችን በራብ ደክመን ዝለናል፤ አባትህ ግን ‘በዛሬው ዕለት ምንም ዐይነት ምግብ የሚመገብ ሰው የተረገመ ይሁን’ ሲል በብርቱ አስጠንቅቆናል” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሕዝቡም አንድ ሰው መልሶ፦ አባትህ፦ ዛሬ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን መሐላ አምሎአቸዋል አለው፥ ሕዝቡም ደከሙ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 14:28
4 Referencias Cruzadas  

ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም።


ዮና​ታን ግን አባቱ ሕዝ​ቡን ባማለ ጊዜ አል​ሰ​ማም ነበር፤ እር​ሱም በእጁ ያለ​ች​ውን በትር አን​ሥቶ ጫፍ​ዋን ወደ ወለ​ላው ነከረ፤ እጁ​ንም ወደ አፉ አደ​ረገ፤ ዐይ​ኑም በራ።


ዮና​ታ​ንም “አባቴ ምድ​ሪ​ቱን አስ​ቸ​ገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀ​ምስ ዐይኔ እንደ በራ እዩ፤


ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ንገ​ረኝ” አለው፤ ዮና​ታ​ንም፥ “በእጄ ባለው በበ​ትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በር​ግጥ ቀም​ሻ​ለሁ፤ እነ​ሆኝ፥ እሞ​ታ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው።