እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ።
1 ሳሙኤል 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሳሙኤልን፥ “ግፍም አላደረግህብንም፤ የቀማኸን የለም፤ አላሠቃየኸንም፤ ከእኛም ከማንም እጅ ምንም አልወሰድህም” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “አላታለልኸንም ወይም ግፍ አልሠራህብንም፤ ከማንም እጅ አንዳች ነገር አልተቀበልህም” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “አላታለልኸንም ወይም ግፍ አልሠራህብንም፤ ከማንም እጅ አንዳች ነገር አልተቀበልህም” ብለው መለሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “ከቶ አላታለልከንም፤ አልጨቈንከንም፤ ከማንም ሰው ምንም ነገር አልወሰድክም” ሲሉ መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አልሸነገልኸንም፥ ግፍም አላደረግህብንም፥ ከሰውም እጅ ምንም አልወሰድህም አሉ። |
እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ።
ለድሜጥሮስ ሁሉ ይመሰክሩለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም ደግሞ እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችንም እውነት እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”
ሳሙኤልም፥ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ በዚህች ቀን እግዚአብሔር ምስክር ነው፤ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው” አላቸው፤ እነርሱም፥ “አዎ ምስክር ነው” አሉ።