አዲስ ልብንም እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
1 ሳሙኤል 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሳሙኤልም ዘንድ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት፤ በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ሁሉ ደረሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሳኦልን ልብ ለወጠው፤ ምልክቱም ሁሉ በዚያ ዕለት ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ፥ እግዚአብሔር የሳኦልን ልብ ለወጠው፤ ምልክቱም ሁሉ በዚያ ዕለት ተፈጸመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ከሳሙኤል ተለይቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር ሳኦልን ሌላ አዲስ ሰው አደረገው፤ ሳሙኤል በምልክት የነገረውም ሁሉ በዚያን ቀን ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሳሙኤልም ዘንድ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት፥ በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ሁሉ ደረሱለት። |
አዲስ ልብንም እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን በትሩን ዘርግቶ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ አስነካ፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ በላች። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዐይኖቹ ተሰወረ።
የሚናገሩትንም አድምጣቸው፤ ከዚያም በኋላ እጆችህ ይበረታሉ፤ ወደ ሰፈርም ትወርዳለህ” አለው። እርሱም ከሎሌው ፋራን ጋር ከሰፈሩ በአንድ ወገን የአምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈረበት ወረደ።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።
የታመነ ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ በልቤም፥ በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፤ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።