አበኔርም ደግሞ በብንያም ልጆች ጆሮ ተናገረ፤ አበኔርም ደግሞ በእስራኤልና በብንያም ቤት ሁሉ መልካም የነበረውን ለዳዊት ሊነግረው ወደ ኬብሮን ሄደ።
1 ሳሙኤል 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ አቀረበ፤ ዕጣውም በብንያም ወገን ላይ ወደቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ ባቀረበ ጊዜ፣ የብንያም ነገድ ተመረጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ ባቀረበ ጊዜ፥ የብንያም ነገድ ተመረጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱ ነገድ ወደ ፊት እንዲቀርብ አደረገ፤ የብንያምም ነገድ በዕጣ ተመረጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ አቀረበ፥ ዕጣውም በብንያም ነገድ ላይ ወደቀ። |
አበኔርም ደግሞ በብንያም ልጆች ጆሮ ተናገረ፤ አበኔርም ደግሞ በእስራኤልና በብንያም ቤት ሁሉ መልካም የነበረውን ለዳዊት ሊነግረው ወደ ኬብሮን ሄደ።
እርስ በርሳቸውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ አገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።
ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በዘመኑ ሁሉ ይጋርደዋል፤ በትከሻውም መካከል ያድራል።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን እግዚአብሔርን ንቃችሁ፦ ‘እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ” አላቸው።
የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፤ ዕጣውም በማጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማጥርንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፤ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለገውም፤ አላገኘውምም።
ሳኦልም እግዚአብሔርን፥ “የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያህ ዛሬ ያልመለስህልኝ ስለ ምንድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮናታንም እንደ ሆነች አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተናገር። ዕጣው ይህን የሚገልጥ ከሆነ ለሕዝብህ ለእስራኤል እውነትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮናታንና በሳኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝቡም ነፃ ወጣ።