1 ነገሥት 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል እንጂ ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ቤተ መቅደሱን የምትሠራው አንተ አይደለህም፤ ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ ከአብራክህ የሚከፈለው፣ የገዛ ልጅህ ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ለስሜ ቤት የሚሠራው ከአንተ የሚወለደው ልጅ እንጂ አንተ አይደለህም’። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እርሱን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው እንጂ አንተ አይደለህም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ቤተ መቅደሴን ይሠራል’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል እንጂ ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤’ አለው። |
እግዚአብሔርም አባቴን ዳዊትን፥ “ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በልብህ አስበሃልና ይህን በልብህ ማሰብህ መልካም አደረግህ።
“ሂድ፥ ለአገልጋዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጡ እኖርበት ዘንድ ቤትን የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል።