በታላቁም አደባባይ ዙሪያ የነበረው ቅጥር እንደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ውስጠኛው አደባባይ ቅጥርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተጠረበ ድንጋይ አንዱም ወገን በዝግባ ሳንቃ ተሠርቶ ነበር።
1 ነገሥት 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዕማዱም ያሉበትን ቤት ሠራ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእርሱም ፊት ደግሞ ታላቅ አዕማድና መድረክ ያሉበት ወለል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን፣ “ባለብዙ ምሰሶ አዳራሽ” የተባለ ቤት ሠራ፤ የዚህም ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፣ ወርዱ ሠላሳ ክንድ፣ ነበር፤ በስተ ፊት በኩልም ጣራ ያለውና በአዕማድ የተደገፈ መመላለሻ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ባለ ብዙ ምሰሶዎች” ተብሎ የተጠራው አዳራሽ ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሜትር፥ ወርዱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፤ በብዙ ምሰሶዎች የተደገፈና ጣራ የተሠራለት መመላለሻ ታዛም ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ባለ ብዙ ምሰሶዎች” ተብሎ የተጠራው አዳራሽ ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሜትር፥ ወርዱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፤ በብዙ ምሰሶዎች የተደገፈና ጣራ የተሠራለት መመላለሻ ታዛም ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዕማዱም ያሉበትን ቤት ሠራ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእርሱም ፊት ደግሞ አዕማድና መድረክ ያሉበት ወለል ነበረ። |
በታላቁም አደባባይ ዙሪያ የነበረው ቅጥር እንደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ውስጠኛው አደባባይ ቅጥርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተጠረበ ድንጋይ አንዱም ወገን በዝግባ ሳንቃ ተሠርቶ ነበር።
ደጆቹ፥ መቃኖቹና የታችኛውና የላይኛው መድረኮች ሁሉ አራት ማዕዘን ነበሩ፤ መስኮቶቹም በሦስት ወገን ሆነው ፊት ለፊት ይተያዩ ነበር።