1 ነገሥት 7:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱንም ኩሬ፥ ከኩሬውም በታች የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን በሬዎች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዳውና ከሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፥ ገንዳውን ደግፈው የሚይዙ የዐሥራ ሁለቱ በሬዎች ቅርጾች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፥ ገንዳውን ደግፈው የሚይዙ የዐሥራ ሁለቱ በሬዎች ቅርጾች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱንም ኵሬ፥ ከኵሬውም በታች የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን በሬዎች፥ |
ኩሬውም በዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱም ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር። ኩሬውም በላያቸው ነበረ፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተውስጥ ነበረ።