በየመቀመጫዎቹም ሁሉ አራት የናስ መንኰራኵሮች ነበሩባቸው፤ መንኰራኵሮቹም የሚዞሩበትን የናስ ወስከምት ሠራ፤ ከመታጠቢያውም ሰን በታች በአራቱ ማዕዘን በኩል አራት በምስል የፈሰሱ እግሮች ነበሩ።
1 ነገሥት 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየአንዳንዱም መቀመጫ በአራቱ ማዕዘን በኩል አራት ደገፋዎች ነበሩ፤ ደገፋዎቹም ከመቀመጫው ጋር ተጋጥመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ወጣ ያለ እጀታ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ማእዘኖች በየግርጌአቸው ከእነርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከነሐስ የተሠሩ አራት መደገፊያዎች ነበሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ማእዘኖች በየግርጌአቸው ከእነርሱው ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከነሐስ የተሠሩ አራት መደገፊያዎች ነበሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእያንዳንዱም መቀመጫ በአራቱ ማዕዘን በኩል አራት ደገፋዎች ነበሩ፤ ደገፋዎቹም ከመቀመጫው ጋር ተገጥመው ነበር። |
በየመቀመጫዎቹም ሁሉ አራት የናስ መንኰራኵሮች ነበሩባቸው፤ መንኰራኵሮቹም የሚዞሩበትን የናስ ወስከምት ሠራ፤ ከመታጠቢያውም ሰን በታች በአራቱ ማዕዘን በኩል አራት በምስል የፈሰሱ እግሮች ነበሩ።
የመንኰራኵሮቹም ሥራ እንደ ሰረገላ መንኰራኵር ሥራ ነበረ፤ ወስከምቶቹና የመንኰራኵሮቹ ክፈፍ፥ ቅትርቶቹም፥ ወስከምቱ የሚገባበት ቧምቧ ሁሉ በምስል የፈሰሰ ነበር።
በመቀመጫውም ራስ ላይ ስንዝር የሚሆን ድቡልቡል ነገር ነበረ፤ በመቀመጫውም ላይ የነበሩ መያዣዎችና ሰንበሮች ከእርሱ ጋር ይጋጠሙ ነበረ፤ ከላይም ክፍት ነበረ፤