ኢዮስያስ ግን ይዋጋው ዘንድ ተጽናና እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በእግዚአብሔርም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ በመጊዶንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።
1 ነገሥት 22:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢያትም ሁሉ እንዲህ ብለው ትንቢት ተናገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ዝመት፤ እግዚአብሔርም ይረዳሃል። ሶርያውያንንና ንጉሣቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩትም ነቢያት ሁሉ፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና፣ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ዝመትባት” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ ጌታም ድልን ይሰጥሃል” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ይሰጥሃል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢያትም ሁሉ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሂድና ተከናወን፤” እያሉ እንዲህ ትንቢት ይናገሩ ነበር። |
ኢዮስያስ ግን ይዋጋው ዘንድ ተጽናና እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በእግዚአብሔርም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ በመጊዶንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።
አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ እናጠፋችሁ ዘንድ ወደዚህ ሀገር ዘምተናልን? እግዚአብሔር፦ ወደ ሀገራቸው ዘምታችሁ አጥፉአቸው” አለን።
እግዚአብሔር ሳይልካቸው፦ እግዚአብሔር ይላል የሚሉ ሰዎች ሐሰትን ያያሉ፤ ከንቱን ያምዋርታሉ፤ ቃሉንም ማጽናት ይጀምራሉ።