ንጉሡ ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች ጠራ፤ የገባዖን ሰዎችም ከአሞራውያን የተረፉ ነበሩ እንጂ ከእስራኤል ልጆች ወገን አልነበሩም፤ የእስራኤልም ልጆች ምለውላቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእስራኤል ልጆችና ለይሁዳ ስለ ቀና ሊገድላቸው ወድዶ ነበር።
1 ነገሥት 2:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን መሐላ፥ እኔም ያዘዝሁትን ትእዛዝ ስለምን አልጠበቅህም?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ለእግዚአብሔር የማልኸውን መሐላ ያልጠበቅኸውና እኔም የሰጠሁህን ትእዛዝ ያልፈጸምኸው ለምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ታዲያ፥ በጌታ ስም ከማልክ በኋላ ለምን መሐላውን አልጠበቅህም? ያዘዝኩህን ትእዛዝስ ለምን አላከበርክም? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ታዲያ፥ በእግዚአብሔር ስም ከማልክ በኋላ የእግዚአብሔርን መሐላ ለምን አልጠበቅህም? ትእዛዜንስ ስለምን አላከበርክም? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን መሐላ እኔስ ያዘዝሁህን ትእዛዝ ስለ ምን አልጠበቅህም?” አለው። |
ንጉሡ ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች ጠራ፤ የገባዖን ሰዎችም ከአሞራውያን የተረፉ ነበሩ እንጂ ከእስራኤል ልጆች ወገን አልነበሩም፤ የእስራኤልም ልጆች ምለውላቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእስራኤል ልጆችና ለይሁዳ ስለ ቀና ሊገድላቸው ወድዶ ነበር።
ንጉሡም ልኮ ሳሚን አስጠራና፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ለመሄድ በምትወጣበት ቀን ፈጽመህ እንድትሞት ዕወቅ ብዬ በእግዚአብሔር አላስማልሁህምን? ወይስ አላስመሰከርሁብህምን?
ንጉሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአባቴ በዳዊት ላይ የሠራኸውን፥ ልብህም ያሰበውን ክፋት ሁሉ ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም ክፋትህን በራስህ ላይ ይመልሳል።
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።