ሳሚም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ የተናገርኸው ቃል መልካም ነው፤ አገልጋይህም እንዲሁ ያደርጋል” አለው፤ ሳሚም በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመት ተቀመጠ።
1 ነገሥት 2:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስት ዓመትም በኋላ ከሳሚ አገልጋዮች ሁለቱ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ መዓካ ልጅ ወደ አንኩስ ኰበለሉ፤ ለሳሚም፥ “እነሆ፥ አገልጋዮችህ በጌት ናቸው” ብለው ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሦስት ዓመት በኋላ ግን፣ ከሳሚ አገልጋዮች ሁለቱ ወደ ጋት ንጉሥ፣ ወደ መዓካ ልጅ ወደ አንኩስ ኰበለሉ፤ ለሳሚም፣ “እነሆ፣ አገልጋዮችህ በጋት ናቸው” ተብሎ ተነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሺምዒ አገልጋዮች የማዕካ ልጅ ወደ ሆነው አኪሽ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጋት ንጉሥ ኰብልለው ሄዱ፤ ሺምዒም ባርያዎቹ በጋት መኖራቸው ተነገረው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሺምዒ አገልጋዮች የማዕካ ልጅ ወደ ሆነው አኪሽ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጋት ንጉሥ ኰብልለው ሄዱ፤ ሺምዒም ባሪያዎቹ በጋት መኖራቸው ተነገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት ዓመትም በኋላ ከሳሚ ባሪያዎች ሁለቱ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ መዓካ ልጅ ወደ አንኩስ ኮበለሉ፤ ሳሚንም “እነሆ፥ ባሪያዎችህ በጌት ናቸው፤” ብለው ነገሩት። |
ሳሚም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ የተናገርኸው ቃል መልካም ነው፤ አገልጋይህም እንዲሁ ያደርጋል” አለው፤ ሳሚም በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመት ተቀመጠ።
ሳሚም ተነሣ፤ አህያውንም ጭኖ አገልጋዮቹን ይሻ ዘንድ ወደ ጌት ወደ አንኩስ ዘንድ ሄደ፤ ሳሚም ሄዶ አገልጋዮቹን ከጌት አመጣ።