1 ነገሥት 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ እንደ ያዘ ሰማ፤ ንጉሥ ሰሎሞንም ወደ ኢዮአብ እንዲህ ሲል ላከ፤ “በመሠዊያው ቀንድ የተማጠንህ ምን ሆነህ ነው?” ኢዮአብም፥ “ፈርቼሃለሁና በእግዚአብሔር ተማጠንሁ” አለ። ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በንያስን ልኮ፥ “ሂድ ግደልና ቅበረው” ብሎ አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መሆኑን ንጉሥ ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ “ሂድና ግደለው!” ብሎ አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብ ወደ ጌታ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ ወደ ተቀደሰ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሠዊያውን እንደ ያዘ ሰማ፤ ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በናያስን “ሂድ፤ ውደቅበት፤” ብሎ አዘዘው። |
የዮዳሄ ልጅ በንያስም ወደ ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን መጥቶ፥ “ንጉሡ፦ ውጣ ይልሃል” አለው፤ ኢዮአብም፥ “በዚህ እሞታለሁ እንጂ አልወጣም” አለ። የዮዳሄ ልጅ በንያስም፦ ተመልሶ “ኢዮአብ የተናገረው ቃል፥ የመለሰልኝም እንዲህ ነው” ብሎ ለንጉሡ ነገረው።
ንጉሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገረህ አድርግ፤ ገድለህም ቅበረው፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቃለህ።
ሽማግሌውንና ጎበዙን፥ ድንግሊቱንም፥ ሕፃናቱንና ሴቶቹን፥ ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወደ አለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ” አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?