1 ነገሥት 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሰሎሞን የዮዳሄን ልጅ በናያስን ላከ፤ እርሱም አረደው፤ ያንጊዜም አዶንያስ ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ በናያስም አዶንያስን መትቶ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ አዶንያስን ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ አዶንያስን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን የዮዳሄን ልጅ በናያስን ላከ፤ እርሱም ወደቀበት፤ ሞተም። |
ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጤያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘለዓለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
ዳዊትም ጐልማሶቹን አዘዘ፤ ገደሉአቸውም፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴን ራስ ግን ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት።
ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ እንደ ያዘ ሰማ፤ ንጉሥ ሰሎሞንም ወደ ኢዮአብ እንዲህ ሲል ላከ፤ “በመሠዊያው ቀንድ የተማጠንህ ምን ሆነህ ነው?” ኢዮአብም፥ “ፈርቼሃለሁና በእግዚአብሔር ተማጠንሁ” አለ። ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በንያስን ልኮ፥ “ሂድ ግደልና ቅበረው” ብሎ አዘዘው።
ንጉሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገረህ አድርግ፤ ገድለህም ቅበረው፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቃለህ።
እነርሱም፥ “አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል” አሉት። ሶምሶንም፥ “እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ፤ ለእነርሱም አሳልፋችሁ ስጡኝ፤ እናንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላቸው።
ሳሙኤልም አጋግን፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ ወጋው።