1 ነገሥት 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ እንደ ያዘ ሰማ፤ ንጉሥ ሰሎሞንም ወደ ኢዮአብ እንዲህ ሲል ላከ፤ “በመሠዊያው ቀንድ የተማጠንህ ምን ሆነህ ነው?” ኢዮአብም፥ “ፈርቼሃለሁና በእግዚአብሔር ተማጠንሁ” አለ። ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በንያስን ልኮ፥ “ሂድ ግደልና ቅበረው” ብሎ አዘዘው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መሆኑን ንጉሥ ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ “ሂድና ግደለው!” ብሎ አዘዘው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ኢዮአብ ወደ ጌታ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ኢዮአብ ወደ ተቀደሰ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሠዊያውን እንደ ያዘ ሰማ፤ ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በናያስን “ሂድ፤ ውደቅበት፤” ብሎ አዘዘው። Ver Capítulo |