1 ነገሥት 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም፥ “ከአንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ” አለ፤ እርስዋም፥ “ተናገር” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “የምነግርሽ ጕዳይ አለኝ” አላት። እርሷም፣ “ዕሺ ተናገር” ብላ መለሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጠል አድርጎም “እኔ የምጠይቅሽ ጉዳይ አለኝ” አላት። እርሷም “ጉዳይህ ምንድነው?” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጠል አድርጎም “እኔ የምጠይቅሽ ጉዳይ አለኝ” አላት። እርስዋም “ጉዳይህ ምንድን ነው?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “በሰላም ነው፤” አለ። ደግሞም “ከአንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ፤” አለ፤ እርስዋም “ተናገር፤” አለች። |
የአጊት ልጅ አዶንያስም ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ፤ ሰገደላትም፤ እርስዋም፥ “ወደ እኔ መምጣትህ በሰላም ነውን?” አለችው። እርሱም፥ “በሰላም ነው” አለ።
እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።